አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የፓኪስታን ብሔራዊ ሸንጎ ሊቀመንበር ሰይድ ዩሱፍ ራዛ ጊላኒ በኢትዮጵያ ስኬታማ የሆነውን የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር መሠረት ያደረገውን የፓኪስታን ሀገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ ዘመቻ አስጀምራለሁ አሉ፡፡
ሊቀመንበሩ በፓኪስታን ከኢትዮጵያ ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ጀማል በከር (ዶ/ር) ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡
የፓኪስታን ብሔራዊ ሸንጎ ሊቀመንበሩ በዚሁ ወቅት÷ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ በኢትዮጵያ ስላመጣው ለውጥ አድናቆታቸውን ገልጸዋል።
በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ራዕይ እና ስኬት መደነቃቸውን ገልጸው÷ ይህ ተነሳሽነት ችግኞችን መትከል ብቻ ሳይሆን የሀገራችንን የአየር ንብረት እና የሕዝባችንን የወደፊት ተስፋ በዘላቂ ልማት ስለማረጋገጥ ነው ብለዋል።
አምባሳደር ጀማል በከር (ዶ/ር) በበኩላቸው÷ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መሪነት የተወጠነ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብሩ ስኬት ከችግኝ ተከላ የዘለለ መሆኑን አስረድተዋል።
የግብርና እና ደን ልማትን በማበረታታት የምግብ ዋስትናን በማጠናከር፣ የተራቆቱ ሥነምህዳሮችን በመመለስ እና የአፈር መሸርሸርን በመዋጋት ረገድ ወሳኝ ሚና እንደተጫወተ እንደሚገኝም አብራርተዋል።
በተጨማሪም በኢትዮ-ፓኪስታን የፓርላማ ወዳጅነት ቡድን የተቋቋመውን የትብብር ማዕቀፍ ጨምሮ አጠቃላይ የሁለትዮሽ ግንኙነቶች ላይ ውይይት ተደርጓል።
በሁሉም መስኮች ትብብርን ለማፋጠን ስምምነት ላይ የተደረሰ ሲሆን÷ የታቀደው የአረንጓዴ ልማት መርሐ ግብር ለኢትዮ-ፓኪስታን ግንኙነት አዲስና የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ሁነኛ መሠረት እንደሚሆን በፓኪስታን የኢትዮጵያ ኢምባሲ ለፋና ዲጂታል በላከው መረጃ አመላክቷል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!