አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል በአንድ ጀንበር 524 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል ዝግጅት ተጠናቋል አለ የክልሉ ግብርና ቢሮ፡፡
በቢሮው የደን ልማት ዳይሬክተር አቶ ከተማ አብዲሳ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ በዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር እስካሁን 3 ነጥብ 5 ቢሊየን በላይ ችግኞች ተተክሏል።
የችግኝ ተከላውም 788 ሺህ ሄክታር መሬት መሸፈኑን ገልጸው÷ በዚህም ከ10 ነጥብ 6 ሚሊየን በላይ ሕብረተሰብ መሳተፉን ጠቁመዋል።
ሐምሌ 24 በሚካሄደው ሀገራዊ የአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር 524 ሚሊየን ችግኞች ለተከላ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል፡፡
በክልሉ 6 ሺህ 495 ቦታዎች በቴክኖሎጂ መለየታቸውንና በ212 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ለመትከል መታቀዱን ጠቁመው÷ በመርሐ ግብሩ 19 ሚሊየን የሕብረተሰብ ክፍሎች ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ አመላክተዋል።
በሲፈን መገርሳ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!