የሀገር ውስጥ ዜና

የሙሉዓለም ባሕል ማዕከል የባህልና ኪነ ጥበብ ቡድን የአውሮፓ ባህል ፌስቲቫል ስኬታማ ቆይታ…

By Melaku Gedif

July 25, 2025

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሙሉዓለም ባህል ማዕከል የባህልና ኪነ ጥበብ ቡድን በቱርክ በተካሄደው ዓለም አቀፍ የአውሮፓ ባህል ፌስቲቫል የነበራቸውን ቆይታ አጠናቅቀው ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

የባህል ማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር አቶ ገብረማርያም ይርጋ እንዳሉት ÷የባህል ቡድኑ በቱርክ ቆይታው የኢትዮጵያን ባህል፣ ኪነ-ጥበብ እና እሴት በማስተዋወቅ የባህል ዲፕሎማሲ ሥራን አከናውኗል፡፡

በዚህም ኢትዮጵያዊ የባህልና ጥበብ ሥራዎች አድናቆት እና የሜዳልያ ሽልማት የተሰጣቸው ሲሆን÷ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ የዘርፉ መሪዎችና ባለሙያዎች ጋር ትውውቅ መደረጉን ጠቅሰዋል፡፡

የባህል ቡድኑ የተሳተፈበት ፌስቲቫል ባህላዊ እሴቶችን እና ሃብቶችን የማስተዋወቅ እድል መፍጠሩን ነው ያብራሩት፡፡

መድረኩ በቀጣይ ለቱሪዝም እንቅስቃሴ ቱሪስቶች ኢትዮጵያን እንዲጎበኙ የሚያስችሉ ብዙ ዕድሎችን እንደፈጠረም ጠቅሰዋል፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚካሄዱ ፌስቲቫሎች መካፈል የኢትዮጵያን ባህልና ኪነጥበብ በማስተዋወቅና የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ከፍ በማድረግ ለቱሪዝም እንቅስቃሴ የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ መሆኑን አመልክተዋል።

ቱሪዝም በአድናቆት ገበያ ላይ ተመስርቶ የሚቀጥል መሆኑን ጠቅሰው÷ ቡድኑ የኢትዮጵያን ቱሪዝም ዓለም ዓቀፍ ተወዳዳሪነት የሚያሳድጉ አጋዥ ሥራዎች አከናውኗል ብለዋል፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!