አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአማራ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል።
በጉባኤው ማስጀመሪያ ላይ ንግግር ያደረጉት የምክር ቤቱ ዋና አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ በክልሉ እየተከናወኑ ያሉ የሰላምና የልማት ሥራዎች መሻሻልና ውጤታማነት ታይቶባቸዋል ብለዋል።
በክልሉ እየተሻሻለ የመጣውን ሰላምና መረጋጋት በመጠቀም የክልሉና የፌዴራል መንግሥት የልማት ፕሮጀክቶችን የማስፈጸም አቅም ማደጉንም አንስተዋል።
የተቋማት ሪፎርምና አቅም ግንባታ ላይ የተሠራው ሥራ ተቋማዊ አሠራርን በማስፈን ለውጤታማ አፈጻጸም ማገዙንም ጠቁመዋል።
ዴሞክራሲን ያለ ልማት ማሰብ አይቻልም ያሉት አፈ ጉባኤዋ÷ የምክር ቤቱ አባላት የሕዝብ ድምጽ በመሆን፣ መንግሥት እና ሕዝብን ማገናኘትና መራጩን ሕዝብ ተጠቃሚ የማድረግ ሚናቸውን መወጣታቸውን ተናግረዋል።
ምክር ቤቱ ከዛሬ ጀምሮ በሚቀጥሉት አምስት ቀናት በሚኖረው ቆይታ ከሚመለከታቸው አጀንዳዎች መካከል የክልሉ መንግሥት የ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸምን በመገምገም የአዲሱን በጀት ዓመት እቅድ ማጽደቅ ይገኝበታል።
በደሳለኝ ቢራራ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!