ስፓርት

የቁልቢ ገብርኤል የንግስ በዓል በድምቀት ተከብሮ ተጠናቀቀ

By abel neway

July 26, 2025

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቁልቢ ገብርኤል የንግስ በዓል በርካታ የእምነቱ ተከታዮች በተገኙበት በድምቀት ተከብሮ ተጠናቅቋል አለ የበዓሉ የፀጥታ ኮማንድ ፖስት።

የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ፖሊስ መምሪያ አዛዥ እና የኮማንድ ፖስቱ ሰብሳቢ ረዳት ኮሚሽነር ናስር መሀመድ፤ በዓሉ ያለምንም እንከን በስኬት መጠናቀቁን ተናግረዋል።

ህዝብን ያሳተፈ የቅድመ ዝግጅት ስራ መከናወኑ እና የፀጥታ ሀይሉ ከማህበረሰቡ ጋር በመተባበር የሰራው ስራ ለበዓሉ በስኬት መጠናቀቅ ጉልህ አስተዋጽኦ አድርጓል ነው ያሉት።

በንግስ በዓሉ ላይ የትራፊክ አደጋን ጨምሮ ምንም ዓይነት ያጋጠመ ችግር እንዳልነበረ ጠቁመዋል።

በቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል የተከበረው የገብርኤል ዓመታዊ የንግስ በዓል ላይ የእምነቱ ተከታዮች፣ የኃይማኖት አባቶች፣ ቱሪስቶችን ጨምሮ በርካታ እንግዶች ታድመዋል።

በተስፋዬ ኃይሉ