አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ላይ የተከሰተውን የእሳት አደጋ መቆጣጠር ተችሏል።
አደጋው ከቀኑ 8:00 ሰዓት አካባቢ የተከሰተው የእሳት አደጋ መንስኤው እየተጣራ ይገኛል።
እሳቱን ለመቆጣጠር ሕብረተሰቡ እና የጸጥታ አካላት የተቀናጀ ብርቱ ጥረት ያደረጉ ሲሆን፤ በአደጋው የሆስፒታሉ ቀዶ ሕክምና፣ የውስጥ ደዌ ሕክምና እና ተመላላሽ ሕክምና ክፍሎች ላይ ጉዳት መድረሱ ተጠቁሟል።
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በቀድሞ ስሙ ኦቶና ሆስፒታል አንጋፋ እና ከወላይታ ዞን ውጪ በአጎራባች ዞኖች ላሉ ነዋሪዎች ጭምር አገልግሎት የሚሰጥ ሆስፒታል ነው።
በማቱሳላ ማቴዎስ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!