የሀገር ውስጥ ዜና

የኬንያ እና የዛምቢያ ግብርና ሚኒስትሮች አዲስ አበባ ገቡ

By Yonas Getnet

July 26, 2025

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኬንያ እና የዛምቢያ ግብርና ሚኒስትሮች በሁለተኛው የተባበሩት መንግሥታት የምግብ ሥርዓት ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።

የኬንያ ግብርና እና የእንስሳት ሀብት ሚኒስትር ሙታሂ ካግዌ እና የዛንቢያ ግብርና ሚኒስትር ሪዬብን አር ፊሪ ምቶሎ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ታረቀኝ ቡሉልታ እና የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ሰሃርላ አብዱላሂ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በተመሳሳይ የማሊ የግብርና ሚኒስትር ዳንኤል ሲሞዖን እና የጋምቢያ ግብርና ሚኒስትር ዲንባ ሳቫሊ ማምሻውን አዲስ አበባ ሲገቡ፤ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የፍትህ ሚኒስትር ዴኤታ ኤርሚያስ የማነብርሃን (ዶ/ር) እና የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ እያሱ ኤሊያስ (ፕ/ር) ተቀብለዋቸዋል።

ኢትዮጵያ ከሐምሌ 20 እስከ 22 ቀን 2017 ዓ.ም የተባበሩት መንግሥታት የምግብ ሥርዓት ጉባኤን በአዲስ አበባ ታስተናግዳለች።

ኢትዮጵያ ዘርፈ ብዙ ስኬቶችን በማስመዝገብ የማንሰራራት ጉዞን በጀመረችበት ወቅት በምታስተናግደው በዚህ ጉባኤ፤ በበጋ መስኖ ስንዴ፣ በሌማት ትሩፋት፣ በአረንጓዴ ዐሻራ ያስመዘገበችውን ስኬታማ ድሎ በተሞክሮነት ታቀርባለች ተብሎ ይጠበቃል።