የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከተባበሩት መንግስታት ምክትል ዋና ጸሃፊ ጋር ተወያዩ

By Melaku Gedif

July 27, 2025

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከተባበሩት መንግስታት ምክትል ዋና ጸሃፊ አሚና መሃመድ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ ኢትዮጵያ ለመጪዎቹ ሶስት ቀናት በአዲስ አበባ የሚከናወነውን 2ኛውን የተባበሩት መንግሥታት የምግብ ሥርዓት ጉባዔ በጋራ በማዘጋጀቷ ኩራት ይሰማታል ብለዋል።

ዛሬ ማለዳም የተባበሩት መንግሥታት ምክትል ዋና ፀሐፊ አሚና መሃመድን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው ማነጋገራቸውን ተናግረዋል፡፡

በውይይታቸው በመላው አፍሪካና በተቀረውም ዓለም ዘላቂ፣ አካታችና በተለያዩ ፈተናዎች የማይበገር የምግብ ሥርዓት አስፈላጊነትን ጨምሮ በሌሎች ጉዳዮች ላይ ፍሬያማ ውይይት አድርገዋል፡፡

ኢትዮጵያ በተቀናጁ ፖሊሲዎቿ፣ ለአየር ንብረት ጥበቃ ምላሽ ሰጪ በሆነ የግብርና ሥራዋ ብሎም በምግብ ዋስትና እና ለሁሉም የተመጣጠነ ምግብ በማቅረብ ማኅበረሰብ መር ዘዴዎቿ የምግብ ሥርዓትን ለማሻሻል ባላት ጽኑ አቋምና ተግባር ቀጥላለች ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!