የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከፋኦ ዋና ዳይሬክተር ኩ ዶንግዩ ጋር ተወያዩ

By Melaku Gedif

July 27, 2025

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከዓለም የምግብ እና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) ዋና ዳይሬክተር ኩ ዶንግዩ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷ ከዓለም የምግብ እና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) ዋና ዳይሬክተር ኩ ዶንግዩ ጋር መወያየታቸውን ተናግረዋል፡፡

በዚህ ወቅትም የተባበሩት መንግሥታት የምግብ ጉባዔ በአዲስ አበባ በሚጀምርበት ዕለት የፋኦ ዋና ዳይሬክተር ኩ ዶንግዩ በድጋሚ ወደ ኢትዮጵያ እንኳን ደህና መጡ ብለዋል፡፡

በዘላቂነት የግብርና ልማት እና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ፋኦ የኢትዮጵያ ቁልፍ አጋር ሆኖ ቀጥሏል ሲሉም አስገንዝበዋል።