የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከዩኤንዲፒ የአፍሪካ ቀጣና ዳይሬክተር አሁና ኢዚያኮንዋ ጋር ተወያዩ

By Melaku Gedif

July 27, 2025

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከተባበሩት መንግሥታት ረዳት ዋና ፀሐፊ እና የዩኤንዲፒ የአፍሪካ ቀጣና ዳይሬክተር አሁና ኢዚያኮንዋ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷ የተባበሩት መንግሥታት ረዳት ዋና ፀሐፊ እና የዩኤንዲፒ የአፍሪካ ቀጣና ዳይሬክተር አሁና ኢዚያኮንዋ እንኳን በደህና መጡ ብለዋል።

ዩኤንዲፒ በመላው የአፍሪካ አኅጉር አካታች ልማትን ለማሳደግ፣ ለሰላም ግንባታ እና ፅናት ያለውን ጠንካራ ትብብር በእጅጉ እናደንቃለን ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!