አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቀዳማይ ልጅነት ዕድገት ፕሮግራምን ዋነኛ የትውልድ እና የሀገር ግንባታ ምሶሶ አድርገን በስፋት እየሰራን ነው አሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፡፡
ሎጎ ፋውንዴሽን በክሊንተን ኸልዝ አክሰስ ኢንሼቲቭ በኩል የሕጻናትን የፈጠራና የማሰላሰል አቅም የሚጨምሩ መጫወቻዎችን ለከተማ አስተዳደሩ አበርክቷል፡፡
ከንቲባ አዳነች በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ በአዲስ አበባ የቀዳማይ ልጅነት ዕድገት ፕሮግራምን ዋነኛ የትውልድና የሀገር ግንባታ ምሶሶ በማድረግ በስፋት እየተሰራ ነው፡፡
መርሐ ግብሩ በክህሎት የዳበረ፣ በፈጠራ የጎለበተ፣ አካባቢውን በሚገባ የተረዳና ለሚገጥሙት ፈተናዎች አስቀድሞ ሳይንሳዊ መፍትሔ የሚያበጅ ጠንካራና ሀገር ወዳድ ትውልድ ለመገንባት ያስችላል ነው ያሉት።
ፕሮግራሙ መተግበር ከጀመረ አጭር ጊዜ ቢሆንም በርካታ ሀገራት ከወዲሁ ውጤቱን በመረዳት ልምድ እየቀሰሙበት እና እየደገፉት መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ስጦታዎቹ የአዕምሮ እድገት ውስንነትና የአካል ጉዳት ያለባቸውን ሕጻናት ጭምር ያማከሉ መሆናቸውን አውስተው÷ ለተደረገው ድጋፍ አስተባባሪዎቹን አመስግነዋል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!