የሀገር ውስጥ ዜና

የተባበሩት መንግሥታት ምክትል ዋና ፀሐፊ አሚና መሃመድ (ዶ/ር) በመዲናዋ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ

By Hailemaryam Tegegn

July 27, 2025

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የተባበሩት መንግሥታት ምክትል ዋና ፀሐፊ አሚና መሃመድ (ዶ/ር) እና የሥርዓተ ምግብ ጉባኤ ታሳታፊ ከፍተኛ አመራሮች በአዲስ አበባ ከተማ የተገነቡ የልማት ሥራዎች ጎበኝተዋል፡፡

በጉብኝታቸውም የጉለሌ የተቀናጀ ልማት፣ ለሚ ኩራ የግብርና መሽጫ የገበያ ማዕከል፣ ጤና ጣቢያና ትምህርት ቤት፣ የምገባ ተቋማትን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

በጉለሌ የእንጀራ ማዕከሉ በውስጡ ሁለት የእንጀራ መጋገሪያ ህንጻዎች፣ የህጻናት ማቆያ፣ የእህል ማከማቻ፣ ወፍጮ እንዲሁም ልዩ ልዩ አገልግሎት የሚሰጡ ማዕከላትን ጎብኝተዋል፡፡

ፕሮጀክቶቹ ሴቶችን፣ እናቶችንና ወጣቶች ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑም ነው በጉብኝቱ ወቅት የተገለጸው፡፡

ጉብኝቱ ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እያከናወነቻቸው ያለውን ሂደት በአካል እንዲመለከቱ ለማስቻል የተዘጋጀ ነው።

የጉባኤው ተሳታፊዎች ከጉብኝቱ በኋላ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አከናውነዋል፡፡

በግዛቸው ግርማዬ