የሀገር ውስጥ ዜና

2ኛው የተባበሩት መንግሥታት የምግብ ሥርዓት ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው

By Adimasu Aragawu

July 28, 2025

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 2ኛው የተባበሩት መንግሥታት የምግብ ሥርዓት ጉባኤ የበርካታ ሀገራት መሪዎች በተገኙበት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡

ኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ያከናወነቻቸው ተግባራትን በጉባኤው መክፈቻ ላይ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አካፍላለች።

የምግብ ስርዓት ጉባኤው በሐምሌ 2015 ዓ.ም በጣልያን ሮም በተካሄደው የመጀመሪያው የምግብ ስርዓት ጉባኤ ላይ የተገቡ ቃሎች ትግበራ ሂደትን መነሻ በማድረግ የሚካሄድ ነው።

በመንግስታት፣ የምግብ አምራቾች፣ የንግድ ማህበረሰቡና ሌሎች ባለድርሻ አካላት መካከል ያለውን አጋርነት ማጠናከር ሌላኛው የጉባኤው አጀንዳ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

በጉባኤው ላይ ሀገራት የምግብ ስርዓት ትራንስፎርሜሽንን አስመልክቶ ያገኟቸውን ስኬቶችና ያጋጠሟቸው ተግዳሮቶች ላይ ሪፖርት ያቀርባሉ።

ለምግብ ስርዓት ሽግግር የፋይናንስ አማራጮችን ማስፋትና የኢንቨስትመንት መጠንን መጨመር በሚቻልበት ሁኔታ ላይም በጉባኤው ይመከራል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!