አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የተመረቱ ተኪ ምርቶች 4 ነጥብ 3 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላርን ማዳን ችለዋል አለ።
በማኒስቴሩ የተኪ ምርቶች ተወዳዳሪነት ሥራ አስፈፃሚ መሣይነህ ውብሸት ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንዳሉት፤ በአሁኑ ወቅት ተኪ ምርቶች ለሀገር ኢኮኖሚ ወሳኝ ድርሻ እየተወጡ ነው።
ለኮሪደር ልማቱ የሚያገለግሉ ስማርት ፖሎችን፣ ትራንስፎርመሮችን፣ የተለያዩ የኤሌክትሪክ ገመዶችን እና መሠል ግብዓቶችን በተኪ ምርቶች ማሟላት እየተቻለ ነው ብለዋል።
ለተኪ ምርቶች የተሰጠው ትኩረት የኢንዱስትሪዎች የእርስ በርስ ትስስር እንዲጠናከር ምቹ ሁኔታ መፍጠሩንም ተናግረዋል።
በተያዘው በጀት ዓመት 5 ነጥብ 7 ቢሊየን ዶላር በተኪ ምርቶች አማካኝነት ለማዳን ዕቅድ መያዙን አቶ መሣይነህ ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ባመጣው ውጤት የተኪ ምርቶች የሀገር ውስጥ የገበያ ድርሻ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱንም አንስተዋል።
በሰለሞን ይታየው
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!