ዓለምአቀፋዊ ዜና

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ከሶማሊያ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

By Abiy Getahun

July 28, 2025

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ ከሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱ ወቅት ሊቀመንበሩ፤ የሶማሊያን የሰላም መንገድ ለመደገፍ ህብረቱ ያለውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።

ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ በበኩላቸው ለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል እና የአፍሪካ ህብረት ቀጣይ ድጋፍ አድናቆታቸውን መግለጻቸውን የህብረቱ መረጃ አመላክቷል።

ኢትዮጵያ ከጣሊያን እና ከተባበሩት መንግስታት ጋር በመተባበር ያዘጋጀችው ሁለተኛው የምግብ ሥርዓት ጉባኤ ላይ የታደሙት የሶማሊያ ፕሬዚዳንት በጉባኤው፤ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ዓለም አንድ ላይ የሚቆምበት ወቅት መሆኑን አንስተዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!