አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ “በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ ማለዳ ከከተማ አስተዳደሩ ኮሙኒኬሽን እና ሚዲያ ባለሙያዎች ጋር የችግኝ ተከላ አካሂደዋል።
ከንቲባዋ ከባለሙያዎቹ ጋር በመሆን በቀበና ወንዝ ዳርቻ ነው የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ያከናወኑት።
የሚዲያና የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች በኢትዮጵያውያን በጎ የሆነን ሀሳብ የሚያሰርጹ መሆናቸውን ያነሱት ከንቲባ አዳነች÷ አሁንም ስራችውን እንዲያጠናክሩ ማሳሰባቸውን የከተማ አስተዳደሩ ኮሙኒኬሽን ለፋና ዲጂታል ገልጿል።
ዛፍ መትከል የዛሬ ብቻ ሳይሆን የነገም ተስፋችን እንዲሁም የምግብ ዋስትናችንን ለነገው ትውልድ የምናረጋግጥበት በመሆኑ በዛሬው መርሐ ግብር የተሳተፋችሁ ከመትከል ባሻገር መልካም ሀሳብ የምታሰርፁ ናችሁና ችግኞችን ከመትከል ባሻገር ትውልድን የማነፅ ስራ እንድትሰሩ ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!