አዲስ አበባ፣ሐምሌ 22፣2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢንተርፕራይዞችን ውጤታማነት የሚጨምሩ ስራዎች ተከናውነዋል አለ የከተማ አስተዳደሩ ስራና ክህሎት ቢሮ።
በቢሮው የስራ ስምሪት አገልግሎት ዳይሬክተር ሰብሀዲን ሱልጣን ለፋና ሚዳያ ኮርፖሬሽን እንዳሉት÷ ለኢንተርፕራይዞች ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር በተሰራው ስራ በበጀት ዓመቱ ለ2 ሺህ 250 ኢንተርፕራይዞች መስሪያ ቦታ ተሰጥቷቸዋል፡፡
የብድር አቅርቦትን በማስፋት ከ3 ቢሊየን ብር በላይ ለ7 ሺህ 500 ኢንተርፕራይዞች ብድር መሰጠቱን አንስተው÷ ከ12 ሺህ በላይ አዳዲስ ኢንተርፕራይዞችን በማደራጀት ወደ ሥራ ማስገባት ተችሏል ነው ያሉት።
አሁን ላይ በከተማዋ የሥራ ዕድልን በተለያዩ ዘርፎች በመፍጠር የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰራ ስለመሆኑ ጠቁመዋል፡፡
በከተማ ግብርና፣ ኢንዱስትሪ እና አገልግሎት ዘርፎች ላይ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።
በሰለሞን ይታየው
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!