አዲስ አበባ፣ሐምሌ 22፣2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ4 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ አግኝቻለሁ አለ፡፡
ኮርፖሬሽኑ የ2017/18 በጀት ዓመት ዕቅድና አፈፃፀም ግምገማ በጅማ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።
የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ በ2017 በጀት ዓመት የተኪ ምርቶች በ11 ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች እና በሁለት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ተመርተዋል፡፡
በተጨማሪም 6 ቢሊየን ብር የሚገመት የገበያ ትስስር ለመፍጠር ታቅዶ 14 ቢሊየን ብር ግምታዊ የገበያ ትስስር መፈጠሩን ተናግረዋል።
ወደ ውጪ ከተላኩ ምርቶች 124 ሚሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱንና ለ48 ሺህ 900 ዜጎች የስራ ዕድል መፈጠሩን ጠቁመዋል፡፡
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የዕቅዱን 99 በመቶ ማሳካት መቻሉን የገለጹት ፍሰሃ (ዶ/ር)÷ በቀጣይ የኢንዲስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን መሠረተ ልማቶችን በማስፋፋት ሰፊ የስራ ዕድል ለመፍጠር በትኩረት ይሰራል ብለዋል።
በበሪሳ ኃ/ማርያም
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.) Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook WMCC TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!