አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በኦሮሚያ ክልል ማያ ከተማ አስተዳደር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አካሂዷል።
የኮርፖሬሽኑ ሠራተኞች ከከተማዋ ነዋሪዎች ጋር በመሆን በባቴ ቀበሌ ቱሉቦ ተራራ ላይ የተለያዩ ሀገር በቀል ችግኞችን ተክለዋል፡፡
የፈዴራል ቤቶችና ኮርፖሬሽን ስራ አስፈፃሚ አቶ ረሻድ ከማል በዚሁ ወቅት እንዳሉት÷ ባለፉት 6 ዓመታት የተተከሉ ችግኞች ተዛብቶ የነበረውን የተፈጥሮ ሀብትና የአየር ንብረት እንዲስተካከል አድርጎታል፡፡
የሚተከሉ ችግኞች የአፈር መሸርሸር እንዳይከሰት እያደረገ መሆኑንም ጠቁመዋል።
ኮርፖሬሽኑ ቤቶችን በዘመናዊ መንገድ ገንብቶ ለተጠቃሚዎች ከማቅረብ በተጨማሪ በችግኝ ተከላና በሌሎች ተግባራት ላይ በመሳተፍ ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገኝም ተናግረዋል።
በምንያህል መለሰ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!