አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በአንድ ጀንበር ከ21 ሚሊየን በላይ ችግኞች ለመትከል ዝግጅት ተደርጓል።
የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ የሺዋስ ዓለሙ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ አረንጓዴ አሻራ የአፈር መከላትን በመከላከል ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ በመገንባት የላቀ አስተዋጽዖ እያበረከተ ይገኛል።
በዘንድሮ መርሐ ግብር የአንድ ጀንበር ዘመቻ ከ21 ሚሊየን በላይ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞችን በ654 የተከላ ሳይቶች ከ7 ሺህ 924 በላይ ሄክታር መሬት ላይ ለመትከል ዝግጅት መደረጉን ጠቁመዋል።
በዚህም ‘‘በመትከል ማንሰራራት’’ በሚል መሪ ሐሳብ እንደ ሀገር ሐምሌ 24 በሚካሄደው የአንድ ጀንበር ተከላ መርሐ ግብር የደን፣ ጥምር ደንና ሌሎች የአፈር ለምነትን የሚጠብቁና የደን ልማት እጽዋት ችግኞች ይተከላሉ ብለዋል።
ለአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላ ዘመቻ የችግኝ እና የጉድጓድ ዝግጅት መከናወኑን አንስተው÷ በዕለቱ 1 ሚሊየን 42 ሺህ 132 ሕዝብ ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ አብራርተዋል።
ሕብረተሰቡ በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ተሳትፎ በማድረግ አሻራውን እንዲያሳርፍ ጥሪ አቅርበዋል።
በአድማሱ አራጋው
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.) Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook WMCC TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!