አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል አሮጌ ተሽከርካሪ፣ ሞተር ሳይክል እና ብረታ ብረቶችን በሽያጭ በማስወገድ ከ162 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ተደርጓል፡፡
የክልሉ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ ም/ዋና ዳይሬክተርና የንብረት አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ አቶ ይልማ ወየሳ እንዳሉት÷ በ2017 በጀት ዓመት ያለ አገልግሎት የተቀመጡ ተሽከርካሪዎችና ሞተር ሳይክሎችን በመለየት የቴክኒክ ፍተሻ ተከናውኗል።
በዚህም በ132 የመንግስት ተቋማት እና የልማት ድርጅቶች ውስጥ አገልግሎት የማይሰጡ ተሽከርካሪ፣ ሞተር ሳይክሎች እና ቁርጥራጭ ብረቶችን በመለየት በግልፅ ጨረታ በሽያጭ የማስወገድ ስራ ተሰርቷል ነው ያሉት፡፡
በተከናወነ የሽያጭ ተግባር 162 ሚሊየን 220 ሺህ 92 ብር ወደ ክልሉ መንግስት ካዝና እና ወደ ልማት ድርጅቶቹ ካዝና ገቢ መደረጉንም ተናግረዋል፡፡
በክልሉ የንብርት አስተዳደር መመሪያ መሰረት ከተሸጡ የመንግስት መስሪያ ቤት ንብረቶች ውስጥ 50 በመቶ ወደ ክልሉ ካዝና ገቢ የሚደረግ መሆኑን ጠቅሰው÷ ቀሪው ንብረቱን ሲያስተዳድሩ ለነበሩ መስሪያ ቤቶች ገቢ እንደሚደረግ ጠቁመዋል፡፡
በራሳቸው ገቢ የሚተዳደሩ የመንግስት ልማት ድርጅቶችን በሚመለከት ከሽያጭ የሚገኘው ገቢ ሙሉ በሙሉ ለራሳቸው ገቢ እንደሚሆነም አስረድተዋል።
በታሪክ አዱኛ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!