አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጋራ ሀገራዊ ትርክት ለመገንባት የሚዲያው ተቀናጅቶ መስራት ወሳኝ ሚና ይጫወታል አሉ የብልጽግና ፓርቲ ዓለም አቀፍና የሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር)።
የብልፅግና ፓርቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ከፌደራል ተቋማት የሕዝብ ግንኙነት አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር ውይይት እያካሄደ ይገኛል።
ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት÷ አካባቢያዊና ንዑስ ነጣጣይ ትርክቶችን ለመቅረፍ ተቀናጅቶ መስራት ይገባል።
ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምና ሀገራዊ ትርክትን ለማስረፅ ሚዲያዎች መስራት፣ የሰሩትን ደጋግሞ መናገርና የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም ትክክለኛ ሀገራዊ መረጃዎችን ማሰራጨት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።
ሀገርን ለማፍረስ የተሳሳቱ መረጃዎችን በሚያሰራጩ የሀገር ውስጥም ሆነ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ላይ ጥብቅ ክትትል እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።
በዙፋን ካሳሁን
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!