አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት በጅማ ዞን በሻሻ ከተማ ያስገነባውን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በዛሬው ቀን መርቆ ለአገልግሎት ክፍት አድርጓል።
በምርቃት መርሐ ግብሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ተገኝተዋል።
የቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት እየተገበራቸው ካሉ ትላልቅ ፕሮጀክቶች ውስጥ ጥራት ያለው ትምህርት ለሁሉም ተደራሽ ማድረግ መሆኑ ተመላክቷል።
በዚህም ላለፉት 5 ዓመታት በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች 34 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ገንብቶ ከ40 ሺህ በላይ የሚሆኑ ተማሪዎች ትምህርት በአቅራቢያቸው እንዲያገኙ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
የቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት ይህንኑ ተግባር አጠናክሮ በመቀጠል ዛሬ 35ኛውን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስመርቋል።
ትምህርት ቤቶች በአቅራቢያ በማይገኙባቸው ቦታዎች የተገነቡት በትምህርት ዘርፍ ለውጥ ለማምጣት፣ ብቁና ተወዳዳሪ ዜጋን ለማፍራት፣ ትውልድን በትምህርት ለማነጽና የትምህርት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑንም ጽሕፈት ቤቱ አስታውቋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!