የሀገር ውስጥ ዜና

በሲዳማ ክልል በአንድ ጀንበር 8 ሚሊየን ችግኝ ይተከላል

By Abiy Getahun

July 30, 2025

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሲዳማ ክልል እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ በክልሉ በአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር 8 ሚሊየን ችግኝ ለመትከል ዝግጅት ተደርጓል አለ ።

በቢሮው የተፈጥሮ ሀብትና አነስተኛ መስኖ ልማት ዳይሬክተር አቶ በረከት አሰፋ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት፥ በክልሉ የአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ ላይ ከ2 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ሰዎች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል።

ለችግኝ ተከላው 235 ቦታዎች መለየታቸውን፣ የጉድጓድ ዝግጅት መደረጉንና የችግኝ ስርጭት ስራዎች መከናወናቸውን ጠቅሰው፥ ከ2 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በችግኝ ይሸፈናል ብለዋል።

በክልሉ በነገው ዕለት በአንድ ጀንበር ከሚተከሉት 8 ሚሊየን ችግኞች ውስጥ 60 በመቶ የሚሆነው ለአካባቢ ጥበቃ፣ ቀሪው ደግሞ ለምግብነት እና ለደን ሽፋን የሚውሉ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በሲዳማ ክልል በዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር 307 ነጥብ 7 ሚሊየን ችግኝ ለመትከል ታቅዶ በእስካሁን 299 ነጥብ 7 ሚሊየን ችግኞች ተተክለዋል ነው ያሉት።

በክልሉ በነገው ዕለት የሚከናወነውን የአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ ሙሉ በሙሉ ለማሳካት ህብረተሰቡ በነቂስ እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል።

በኃይለማርያም ተገኝ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!