አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በጠንካራ ፉክክር እየተካሄደ ያለው 5ኛው የፋና ላምሮት የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር በነገው ዕለት ቀጥሎ ይካሄዳል።
ባለፈው ሳምንት ከተለዩት የምድብ አንድ ምርጥ አራቱ ጋር ለመቀላቀል ነገ የምድብ ሁለት አምስት ተወዳዳሪዎች ከባድ ትንቅንቅ ያደርጋሉ።
በውድድሩ የምድብ ሁለት አምስት ተወዳዳሪዎች ናሆም ነጋሽ፣ ካሳሁን ዘውዱ፣ ሱራፌል ደረጄ፣ እዮቤል ፀጋዬ እና ናሆም ካሳዬ በቀጥታ ስርጭት ውድድራቸውን ያደርጋሉ።
የዕለት አቀራረብ ላይ መሰረት በሚያደርገው በፋና ላምሮት ውድድር ላይ በዳኞች እና በተመልካቾች ድምፅ በየሳምንቱ አንድ ተሰናባች ይኖራል።
በዕለቱም አንድ ሙዚቀኛ በክብር እንግድነት ይገኛል።
አጠቃላይ ከ3 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ ሽልማት የተዘጋጀለት እና በ13ኛው ሳምንት 4 ምርጥ ተወዳዳሪዎችን ይዞ የፍፃሜ ውድድሩን የሚያካሂደው ፋና ላምሮት የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር የዋንጫ እና የአዲስ ሙዚቃ ሽልማትንም ያበረክታል።
ይህ ደማቅ ውድድር በቀጥታ ስርጭት ፋና ቴሌቪዥንን ጨምሮ በሁሉም የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ማኅበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይተላለፋል።
በለምለም ዮሐንስ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!