ቢዝነስ

ኢትዮ ጅቡቲ ባቡር የአፍሪካ የኢኮኖሚ ትብብር ተምሳሌት ነው – ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር)

By Adimasu Aragawu

August 01, 2025

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮ ጅቡቲ ባቡር የአፍሪካ የኢኮኖሚ ትብብር ተምሳሌት ነው አሉ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር)።

“የባቡር መሠረተ ልማት ለንግድና ቀጣናዊ ትስስር” በሚል ሐሳብ የፓናል ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።

በውይይቱ ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር)፣ የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ፣ የብሄራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምህረቱ፣ የኢትዮ ጅቡቲ ባቡር አክሲዮን ማህበር ዋና ስራ አስፈፃሚ ታከለ ኡማ፣ የጅቡቲ ተወካዮች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት ኢትዮ ጅቡቲ ባቡር የአፍሪካ የኢኮኖሚ ትብብር ተምሳሌት መሆኑን ገልጸው÷ በባቡር ትራንስፖርት ኢትዮጵያን ከአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ጋር ለማስተሳሰር እየተሰራ ነው ብለዋል።

የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ በበኩላቸው÷ የጅቡቲ ወደብ የጭነት ማንሳት አቅምን የሚያሳድግ መሆኑን አንስተው÷ የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣናን ያሳልጣልም ነው ያሉት።

የኢትዮ ጅቡቲ ባቡር አክሲዮን ማህበር ዋና ስራ አስፈፃሚ ታከለ ኡማ የተቋሙን አሰራር ዘመናዊ የማድረግ ሥራዎች በመሰራታቸው ከዘርፋ መገኘት የሚገባንን ጥቅም እያገኘን ነው ብለዋል።

በቅድስት አባተ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!