አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በተጠናቀቀው 2017 በጀት ዓመት በአምራች ኢንተርፕራይዞች ለ201 ሺህ 988 ዜጎች የሥራ ዕድል ተፈጥሯል አለ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት፡፡
የተቋሙ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልፈታ የሱፍ እንዳሉት፥ የአምራች ኢንተርፕራይዞችን የማምረት አቅም ለማሳደግና ተወዳዳሪ ለማድረግ በትኩረት ተሰርቷል፡፡
የማምረቻ ቦታ፣ የፋይናንስና የግብዓት አቅርቦትን ከማሳካት ባለፈ የተለያዩ የተግባር ተኮር ሥልጠናዎች መሰጠታቸውን ተናግረዋል፡፡
በተለይም አዳዲስ ኢንተርፕራይዞች እንዲቋቋሙና ወጪና ተኪ ምርቶች ላይ እንዲሰማሩ አስፈላጊው ድጋፍ ተደርጓል ነው ያሉት።
4 ሺህ 285 አዳዲስ አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞችን ማቋቋም መቻሉንም አንስተዋል፡፡
በሌላ በኩል 12 ሺህ 481 ነባር ኢንተርፕራይዞችን ለማጠናከር ታቅዶ 15 ሺህ በላይ አምራች ኢንተርፕራይዞችን ማጠናከር መቻሉን ጠቅሰዋል።
አዲስ አምራች ኢንተርፕራይዞችን በማቋቋምና ነባሮችን በማጠናከር ለ201 ሺህ 988 ዜጎች የሥራ ዕድል መፈጠሩንም ገልጸዋል።
በቅርቡ በተጀመረው የገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን ኢኒሼቲቭ 381 አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች መቋቋማቸውንም ጠቁመዋል።
በዚህም ለ2 ሺህ 761 ዜጎች የሥራ ዕድል ተፈጥሯል ማለታቸውን የተቋሙ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሮቤል አሕመድ ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል።
በመላኩ ገድፍ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!