አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተደረገ የግብርና ምርታማነትን የማሳደግ ንቅናቄ በርካታ ወረዳዎች አዳዲስ ምርቶችን ማምረት ጀምረዋል።
በክልሉ በተለያዩ ዞኖች የሚገኙ በርካታ ወረዳዎች ከዚህ በፊት የማያመርቷቸውን የጥራጥሬ፣ የሰብል፣ የፍራፍሬ እና የእንስሳት ምርቶች እያመረቱ ነው፡፡
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር እንዳሉት፤ ግብርናን በማዘመን ምርታማነትን ለማሳደግ በስፋት እየተሰራ ነው።
ለክልሉ ሥነ ምህዳር ተስማሚ የሆኑ አዳዲስ ምርቶችን የማስተዋወቅ ሥራ እየተሰራ እንደሆነ ጠቅሰው፤ በዚህም በርካታ ወረዳዎች ከዚህ ቀደም የማያለሟቸውን ምርቶች ወደ ማልማት ገብተዋል ነው ያሉት።
በዚህም ቀደም ሲል በሶስት ወረዳዎች ብቻ ይመረት የነበረው የሙዝ ተክል በአሁኑ ወቅት ወደ 16 ወረዳዎች እንዲስፋፋ መደረጉን ገልጸዋል።
24 ወረዳዎች ፓፓያ 44 ወረዳዎች ደግሞ አቮካዶ ማምረት መጀመራቸውን ጠቁመዋል።
የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማሳደግ በኩታ ገጠም እርሻ ምርታማነትን ማሳደግ ተችሏል ብለዋል።
በታሪክ አዱኛ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!