የሀገር ውስጥ ዜና

በሲዳማ ክልል ህዝብን ተጠቃሚ ያደረጉ የልማት ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ

By Abiy Getahun

August 01, 2025

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል እና የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የተከናወኑ ህዝብን ተጠቃሚ ያደረጉ የልማት ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ አሉ።

በብልጽግና ፓርቲ የሲዳማ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የ2017 የአባላት ማጠቃለያ የውይይት መድረክ በሀዋሳ ተካሂዷል፡፡

በመድረኩ ላይ አቶ ደስታ ሌዳሞ እንዳሉት፤ የክልሉን የመልማት አቅም በመለየት ድህነትን መቀነስ የሚያስችሉ ውጤታማ ተግባራት ተከናውነዋል።

በተለይም የእንስሳት ልማት፣ የማህበራዊ አገልግሎት፣ የቱሪዝም ልማት፣ የሌማት ትሩፋት፣ የኮሪደር ልማት፣ የስንዴ ልማት፣ የፍራፍሬና ሌሎችም የግብርና ልማት ስራዎች ተጨባጭ ውጤት ተመዝግቦባቸዋል ብለዋል።

የክልሉን ነባራዊ ሁኔታ በማገናዘብ የተቀረጹ 6 ኢንሼቲቮች እና 68 ፓኬጆች ከክልሉ አልፎ እንደ ሀገር የህዝብን የልማት ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ጥሩ ማሳያዎች መሆናቸውን ገልጸዋል።

የተገኙ ውጤቶችን በማስፋት፣ ጉድለቶችን በመሙላትና የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ከዳር በማድረስ ለሀገራዊ የብልፅግና ስኬት በጋራ መትጋት ይገባናል ሲሉ አስገንዝበዋል።

በብልጽግና ፓርቲ የሲዳማ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አብረሃም ማርሻሎ በበኩላቸው፤ በፓርቲው ጉባኤ የሰላም ግንባታና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮቸ አጽንኦት ተሰጥቷቸዋል ነው ያሉት።

የክልሉን የኢንቨስትመንትና ቱሪዝም አቅም ማሳደግ ላይ ትኩረት መሰጠቱን መግለጻቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።

ከነዳጅ አቅርቦትና ስርጭት ጋር በተያያዘ የሚነሳውን የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር ለመቅረፍ በተወሰደ ርምጃ ለውጥ መምጣቱን ጠቅሰው፤ ርምጃው በቀጣይም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

የሃሳብ ብዝሃነትን በማክበርና የልማት አንድነትን በማጠናከር የሚስተዋሉ ችግሮችን በዘላቂነት የመፍታትና የማስተካከል ስራ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አረጋግጠዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!