የሀገር ውስጥ ዜና

የኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ 1 ሺህ 973 ተማሪዎቹን አስመረቀ

By Yonas Getnet

August 02, 2025

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን 1 ሺህ 973 ተማሪዎቹን አስመርቋል።

ዩኒቨርሲቲው በመጀመሪያ ዲግሪ 964 እንዲሁም በ2ኛ ዲግሪ 1ሺህ 9 ተማሪዎቹን ነው በዛሬው ዕለት ያስመረቀው።

በምረቃ ሥርዓቱ ላይ የኦሮሚያ ክልል አፈ ጉባኤ ሰኣዳ አብዱርሀማንን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችና የመንግስት ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በደሳለኝ አበራ