ቢዝነስ

በህገወጥ ግብይት የተሳተፉ 354 የነዳጅ ማደያዎች ላይ ክስ ሊመሰረት ነው

By Yonas Getnet

August 02, 2025

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ)በህገወጥ የነዳጅ ግብይት የተሳተፉ 354 ማደያዎች ላይ ክስ እንዲመሰረትባቸው እየተደረገ ነው አለ የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን፡፡

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ደስታው መኳንንት (ዶ/ር) ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት ቆይታ እንዳሉት፥ የነዳጅ ማደያ ከሌለባቸው አካባቢዎች ውጭ ነዳጅ ከማደያ ውጭ እንዳይሸጥ በህግ ተደንግጓል፡፡

ሆኖም የህግ ድንጋጌውን በመተላለፍ በህገወጥ የነዳጅ ግብይት የተሳተፉ 354 ማደያዎች ላይ በክልሎች ክስ እየተመሰረተባቸው ነው ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ ስድስት ኩባንያዎች ለሁለት ወር መታገዳቸውንና ሌሎች ሰባት ኩባንያዎችም የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ተናግረዋል፡፡

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 4 ነጥብ 3 ቢሊየን ሜትሪክ ኪዩብ ነዳጅ ወደ ሀገር ውስጥ መግባቱን ተናግረዋል፡፡

ከዚህም ውስጥ 17 በመቶ የሚሆነው ለኢንዱስትሪዎች፣ ለማዕድን ስራ፣ ለሲሚንቶ ፋብሪካዎች፣ ለመንገድ ግንባታ እንዲሁም ለግብርና ሜካናይዜሽንና ለተለያዩ የልማት ስራዎች ውሏል ነው ያሉት፡፡

በመሳፍንት እያዩ