የሀገር ውስጥ ዜና

የጋምቤላ ክልል የ2018 በጀት ከ12 ቢሊየን ብር በላይ ሆኖ ጸደቀ

By Melaku Gedif

August 02, 2025

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ‎የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት የክልሉን የ2018 ዕቅድ ማስፈፀሚያ በጀት ከ12 ቢሊየን ብር በላይ በማድረግ አጽድቋል።

የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ ኡማን አሙሉ (ዶ/ር) እንዳሉት÷ የክልሉን ወጪ በራስ የገቢ ምንጭ ለመሸፈን አበረታች ጥረት እየተደረገ ይገኛል።

በ2018 ከተያዘው በጀት ውስጥ 7 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር በክልሉ ከሚሰበሰብ ገቢ የሚሸፈን ሲሆን÷ 4 ነጥብ 3 ቢሊየን ብሩ ደግሞ ከፌዴራል መንግስት በድጎማ የሚገኝ ነው ብለዋል፡፡ ‎ ‎በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የተከናወኑ ስኬቶችን በስፋት ለማስቀጠልና የሕዝቡን ጥያቄዎች ለመመለስ በትኩረት እንደሚሰራ አመልክተዋል፡፡

‎ምክር ቤቱ እያካሄደ በሚገኘው 8ኛ መደበኛ ጉባዔ በጀቱን ከመረመረ በኋላ በሙሉ ድምጽ ማጽደቁን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ለፋና ዲጂታል ገልጿል።

ምክር ቤቱ በመጨረሻም የ14 የወረዳ እና የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞችን ሹመት በማጽደቅ ጉባዔውን አጠናቅቋል።

ተሿሚዎቹ የተሰጣቸውን ተልዕኮ በአግባቡ በመወጣት ሕዝቡን በቅንነት እና በታማኝነት ለማገልገል ቃል ገብተዋል፡፡

በዮናስ ጌትነት

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!