አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራው ለማዕድን ዘርፉ ዕድገት ማስፈንጠሪያ ሆኖ አገልግሏል አለ የማዕድን ሚኒስቴር፡፡
የማዕድን ሚኒስትር ሃብታሙ ተገኝ (ኢ/ር) እንዳሉት ÷ በተጠናቀቀው 2017 በጀት ዓመት በማዕድን ዘርፍ ከፍተኛ እና አበረታች ውጤት ተመዝግቧል፡፡
ለዚህ ደግሞ ኢትዮጵያ በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ገቢራዊ ያደረገችው የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም የጎላ አበርክቶ እንዳለው ነው ያስረዱት፡፡
ከወርቅ ምርት የሚገኘውን የውጭ ምንዛሪ ግኝት ከማሳደግ ጀምሮ የማዕድን ዘርፉ ዕድገት ማስፈንጠሪያ ሆኖ ማገልገሉን ተናግረዋል፡፡
የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ለውጭ ገበያ የሚቀርበውን ብቻ ሳይሆን ተኪ ምርቶችን ጭምር በማበረታታት ስኬት የተመዘገበበት መሆኑን አንስተዋል፡፡
ኢትዮጵያ በዘርፉ ላስመዘገበችው ስኬት ከዘርፉ ተዋንያን ጋር የነበራት ትብብርና ቅንጅታዊ አሰራር ሚናው የጎላ እንደነበርም አስታውሰዋል፡፡
ኢትዮጵያ የድንጋይ ከሰል ከውጭ ለማስመጣት እስከ 300 ሚሊየን ዶላር ያስፈልጋት እንደነበር የገለጹት ሚኒስትሩ÷ የድንጋይ ከሰል አቅርቦት እጥረት በመከሰቱ ሲሚንቶ ማምረትና ለገበያ ማቅረብ አስቸጋሪ ነበር ብለዋል፡፡
ይሁን እንጂ በ2017 አራት የድንጋይ ማጠቢያ ፋብሪካዎችን በማስመረቅ የሲሚኒቶ ምርትን አቅርቦት ማሳደግና ዋጋውን መቀነስ መቻሉን ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ በቅርቡ የመጀመሪያውን ምዕራፍ የጋዝ ምርት ለገበያ እንደምታቀርብ ጠቁመው÷ የማዕድን ዘርፉ ለኢኮኖሚ ጥቅም እንዲውል እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡
እንደ ሀገር ድፍድፍ ዘይትን ጨምሮ ጥቅም ላይ ያልዋሉ የማዕድን ሀብቶች እንዳሉና እነዚህን ሃብቶች ለሀገር ጥቅም ማዋል እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
የአፈር ማዳበሪያ ለኢትዮጵያ የህልውና ጉዳይ መሆኑን ያነሱት ሚኒስትሩ÷ ሀገራችን ያላትን ሰፊና ለም የእርሻ መሬት በአግባቡ ጥቅም ላይ ማዋል ይገባል ነው ያሉት፡፡
ለኢትዮጵያ ጋዝ ማውጣት ከሽያጭ ባለፈ በስፋት ጥቅም ላይ የሚውለውን የዩሪያ የአፈር ማዳበሪያ ለማምረት የሚያስችል አቅም መፍጠር እንደሚያስችልመናገራቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!