ዓለምአቀፋዊ ዜና

ሕንድ ከሩሲያ ነዳጅ ዘይት መግዛቴን እቀጥላለሁ አለች

By Melaku Gedif

August 02, 2025

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሕንድ ከሩሲያ ነዳጅ ዘይት መግዛቴን አጠናክሬ እቀጥላለሁ አለች፡፡

አሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቅርቡ ሕንድ ከሩሲያ ነዳጅ ዘይት መግዛቷን እንደምታቆም መናገራቸው ይታወሳል፡፡

የፕሬዚዳንቱን ንግግር ተከትሎም ሕንድ ከሩሲያ ነዳጅ ዘይት መግዛቷን አጠናክራ እንደምትቀጥል ማረጋገጧን የሀገሪቱን ባለስልጣናት ጠቅሶ ኒዮርክ ታይምስ ዘግቧል፡፡