አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አምስተኛው የአፍሪካ የድህረ ምርት ብክነት ቅነሳ ጉባኤ እና አውደ ርዕይ ከመስከረም 6 ጀምሮ በአዲስ አበባ ይካሄዳል።
ጉባኤው እና አውደ ርዕይዩ “ምርትን መጠበቅ፤ የድህረ ምርት ብክነት አስተዳደር መፍትሄዎች ለማይበገር እና ሁሉን አካታች የምግብ ሥርዓት” በሚል መሪ ሐሳብ ነው ለአራት ቀናት የሚካሄደው።
ጉባኤው በአፍሪካ የድህረ ምርት ብክነትን በፍጥነት መቀነስ እንዲሁም ዘላቂ የግብርና እና የምግብ ሥርዓቶችን ማጠናከር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የአፍሪካ ህብረት ይሄን ችግር በተቀናጀ አሰራርና በባለድርሻ አካላት ትብብር በጠንካራ ምላሽ ለመፍታት እየሰራ ይገኛል፡፡
በጉባኤው ድህረ ምርትን የተመለከቱ የተለያዩ ውይይቶች የሚደረጉ ሲሆን÷ የምርምር ውጤቶች እንደሚቀርቡና የተለያዩ የጎንዮሽ ሁነቶችና አውደ ርዕዮች እንደሚካሄዱ ተገልጿል፡፡
ወጣቶችና ሴቶች ድህረ ምርት ብክነትን የሚቀንሱ ሥርዓቶችን ከመዘርጋት አኳያ ያላቸው ሚና ከጉባኤው የትኩረት ማዕከል መካከል ይጠቀሳል።
አርሶ አደሮች፣ ተመራማሪዎች፣ ፖሊሲ አውጪዎች፣ ባለሀብቶች እና የሲቪክ ማህበረሰብ ተቋማትን ጨምሮ ከ400 በላይ ልዑካን በጉባኤው ላይ ይሳተፋሉም ተብሎ ይጠበቃል።
ተሳታፊዎች የዕውቀት እና የቴክኖሎጂ ልምድ ልውውጥ ከማድረጋቸው ባሻገር አፍሪካ የማይበገር ጠንካራ የምግብ ሥርዓት መገንባት በምትችልበት ሁኔታ ላይ ይመክራሉ።
ጉባኤው እና አውደ ርዕዩ አፍሪካ የምግብ ሉዓላዊነትን እና ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ እንደሆነም ተመላክቷል፡፡
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ከልማት አጋሮች፣ ከትምህርት ዘርፍ ተዋንያንና የግሉ ዘርፍ ጋር በመሆን አህጉራዊውን ጉባኤ ማዘጋጀታቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!