አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የሚያዘጋጀው አራተኛው ሀገር አቀፍ የሰላም ጉባኤ በሐረር ከተማ መካሄድ ጀምሯል።
ጉባኤው ሃይማኖት ለሰላም፣ አንድነትና አብሮነት ላይ እየመከረ ሲሆን÷ የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች እና የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍል ተወካዮች ተገኝተዋል።
ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት የሚካሄደው የሰላም ጉባኤ በሀገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት አስተዋጽኦ እንደሚኖረውም ተገልጿል።
ጉባኤው ከዚህ ቀደም በድሬዳዋ፣ ጅማ እና ባሕር ዳር በተካሄዱ የሰላም ጉባኤዎች ሕብረተሰቡ የሰላም ባለቤት እንዲሆን የሚያስችሉ ተግባራት መከናወናቸውም ተመላክቷል።
በጌታሰው የሽዋስ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!