የሀገር ውስጥ ዜና

የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ አባላት በሐረር አረንጓዴ ዐሻራቸውን አኖሩ

By Melaku Gedif

August 04, 2025

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ አባላት በሐረር ከተማ ከመደመር ትውልድ መጽሐፍ ሽያጭ በተገኘ ገቢ በተገነባው ኢኮ ፓርክ አረንጓዴ ዐሻራቸውን አኑረዋል።

በመርሐ ግብሩ የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጠቅላይ ጸሐፊ ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ እና የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት ጉባዔ የበላይ ጠባቂ አባቶች ተወካዮች ተሳትፈዋል፡፡

የጉባዔው አባላት የሐረርን የቱሪስት መስህብነት ለማጉላት ከፍተኛ አቅም ያለውን የኮሪደር ልማትና የጁገል ግንብን ጨምሮ ሌሎች የልማት ሥራዎችንም ተመልክተዋል።

በነገው ዕለት በሐረር ከተማ በሚገኘው ኢማም አሕመድ ስታዲየም የሰላም መልዕክት ያስተላልፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት 4ኛው ሀገር አቀፍ የሰላም ኮንፍረንስ በሐረር ከተማ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!