አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል በተያዘው በጀት ዓመት ከ7 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ህፃናትን በቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራም ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ነው።
የክልሉ ቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራም አስተባባሪ ታምሩ ታደሰ የቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራም በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ይተገበር እንደነበር ገልጸው÷ የኦሮሚያ ክልል ኢኒሼቲቩን በመውሰድ በሁሉም አካባቢዎች እንዲጀመር መወሰኑን ተናግረዋል።
በዚህም ክልሉ በ415 ወረዳዎች 17 ሺህ 200 የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን በመገንባት ፕሮግራሙ ስራ ላይ እንዲውል መደረጉንና በ750 ጤና ጣቢያዎች እና በተወሰኑ ሆስፒታሎች ላይ ስራው መጀመሩን ጠቁመዋል።
የጤና፣ የትምህርት እንዲሁም የሴቶችና ህፃናት ጉዳዮች ቢሮ ጉዳዩን በባለቤትነት እየሰሩ መሆናቸውንም አቶ ታምሩ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ገልጸዋል።
ፕሮግራሙ ከተጀመረ አንድ ዓመት አካባቢ እንደሆነው እና የስትራቴጂክ ፕላን መዘጋጀቱን እንዲሁም የስትሪንግ ኮሚቴ መቋቋሙን አንስተው÷ ክልሉ ካለው ስፋት እና ከበጀት አንፃር ሰፊ ስራ እንደሚጠበቅ አስረድተዋል።
በተያዘው በጀት ዓመት ዕድሜያቸው ከ6 ዓመት በታች የሆኑ 7 ነጥብ 5 ሚሊየን ህፃናትን እና በርካታ የሚያጠቡ እና ነፍሰ ጡር እናቶችን ተደራሽ ለማድረግ መታቀዱን ጠቅሰው÷ እስካሁን ለ4 ነጥብ 5 ሚሊየን እናቶች የአልሚ ምግብ ድጋፍ መደረጉን አመልክተዋል።
በተጨማሪም በ33 ከተሞች የቤት ለቤት የምክር አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነና 11 ሚሊየን ለሚጠጉ ህፃናት እና ወላጆች የምክር አገልግሎት መሰጠቱን ጠቁመዋል።
በመሳፍንት እያዩ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!