አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በተጠናቀቀው 2017 በጀት ዓመት ለአምራች ኢንተርፕራይዞች ከ18 ቢሊየን ብር በላይ የሥራ ማስኬጃ ብድርና የማምረቻ መሳሪያ ተሰራጭቷል፡፡
የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ጳውሎስ በርጋ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ ኢንተርፕራይዞች ከብድርና መስሪያ ቦታ ጋር በተያያዘ የሚያነሷቸውን ጥያቄዎች ለመፍታት እየተሰራ ነው፡፡
በተለይም የዘርፉን አሰራር ሥርዓት ለማሻሻል፣ የማምረት አቅምን ለማሳደግና ጥራት ያለው ምርት ለማምረት በቁርጠኝነት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
ለአምራች ዘርፉ ልዩ ትኩረት መስጠቱን የተናገሩት ም/ዋና ዳይሬክተሩ ÷ በዚህም አስፈላጊው ድጋፍና ክትትል እየተደረገ እንደሚገኝ አንስተዋል፡፡
በ2017 በጀት ዓመት ለ1 ሺህ 740 አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች 11 ነጥብ 38 ሚሊየን ብር በላይ የሥራ ማስኬጃ ብድር መሰራጨቱን ጠቁመዋል፡፡
እንዲሁም ለ1 ሺህ 462 አምራች ኢንተርፕራይዞች 6 ነጥብ 99 ቢሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የማምረቻ መሳሪያዎች ተሰራጭተዋል ነው ያሉት፡፡
በቀጣዩ ዓመት ለኢንተርፕራይዞች የብድር አቅርቦትና የማምረቻ ቦታ ተደራሽነትን ለማስፋት በትኩረት እንደሚሰራም አመልክተዋል፡፡
በመላኩ ገድፍ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!