የሀገር ውስጥ ዜና

በኦሮሚያ ክልል በ14 ዘርፎች የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት እየተከናወነ ነው

By Yonas Getnet

August 06, 2025

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል በ14 ዘርፎች የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በተጠናከረ መልኩ እየተከናወነ ነው አለ የክልሉ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ።

በቢሮው የወጣቶች በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ዳይሬክተር አቶ አሚኖ አማን እንዳሉት÷የዘንድሮው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች እየተከናወነ ይገኛል።

ለመርሐ ግብሩ ስኬታማነት ከክልል ጀምሮ በየደረጃው ባለው መዋቅር ቅንጅት መፈጠሩን ጠቁመው÷ለዚህም በርካታ ወጣቶችን በማንቀሳቀስ ሕዝቡን ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

አገልግሎቱ በ14 ዘርፎችና በ35 የሥራ ዝርዝሮች ላይ በማተኮር እየተከናወነ ሲሆን÷ ዘርፎቹ የሕዝቡን ኑሮ የሚያሻሽሉ እና ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ እንደሚያግዙ ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

በተለይም በአረንጓዴ አሻራ፣ በደም ልገሳ፣ የአቅመ ደካሞች ቤት እድሳትና ግንባታ፣ በሰላም ግንባታ እና ሌሎች ሥራዎች የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ እየተከናወነ እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!