አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ እንደ አዘጋጅ ሀገር በአየር ንብረት ለውጥ የሰራቻቸውን ስራዎች ለተሳታፊዎች ታሳያለች አሉ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴዔታ ስዩም መኮንን፡፡
የጉባኤውን በኢትዮጵያ መዘጋጀት አስመልክቶ መግለጫ የሰጡት ሚኒስትር ዴኤታው፤ ኢትዮጵያ በጉባኤው በአረንጓዴ ዐሻራ፣ በታዳሽ ሀይል አጠቃቀምና እና በሌሎችም ዘርፎች ያስመዘገበቻቸውን ውጤቶችን በተጨባጭ ታሳያለች፡፡
በጉባኤው አፍሪካውያን ለአየር ንብረት ለውጥ የሰሯቸውንና ያስመዘገቧቸውን የመፍትሔ ሀሳቦች ያቀርባሉ ብለዋል።
ጉባዔው በዋናነት አፍሪካውያንን ተጠቃሚ፣ የመፍትሄ አካል እና ወደ መሪነት መድረክ በማምጣት መሰረታዊ ለውጦችን የሚያመጣ ስለመሆኑ አስረድተዋል፡፡
በጉባዔው ላይ የ45 ሀገራት መሪዎች እና ከ25 ሺህ በላይ ተሳተፊዎች ይገኙበታል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ጉባኤው ሲጠናቀቅ አፍሪካውያን በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ በመስማማት የጋራ አቋም ያወጣሉ፡፡
ስምምነቱ በመጪው ህዳር ወር ለሚካሄደው የኮፕ 30 የአየር ንብረት ጉባኤ የአፍሪካውያን አቋም ሆኖ ይቀርባል ነው የተባለው።
ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሕብረት ጋር በመተባበር ሁለተኛውን የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ ከጳጉሜ 3 እስከ 5 ቀን 2017 ዓ.ም የምታስተናግድ ይሆናል፡፡
በእዮናዳብ አንዱአለም
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!