ቢዝነስ

ግብርናውን የሚያዘምኑ ቴክኖሎጂዎችን ወደ ሀገር ለማስገባት እየተሰራ ነው

By Abiy Getahun

August 06, 2025

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ የምግብ ፍጆታዋን ለማሟላት ግብርናውን የሚያዘምኑ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ወደ ሀገር ለማስገባት እየሰራች ነው፡፡

የናሽናል ኤርወይስ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ገዘሀኝ ብሩ እንዳሉት፤ በቅርቡ በግብርና ሚኒስቴር ወደ ሀገር ውስጥ የገቡት የኬሚካል ርጭት ዘመናዊ አውሮፕላኖች ግብርናውን ወደኋላ የጎተተውን የኬሚካል ርጭት ያዘምናሉ።

ዘመናዊ አውሮፕላኖቹ ግብርናውን ለማሳደግ እየተደረገ ያለው ጥረት አንድ አካል መሆኑን ጠቅሰው፤ አርሶ አደሩ በአረም እና በተባይ አማካኝነት የሚያጋጥመውን የምርት መቀነስ ችግር እንደሚፈታ ተናግረዋል።

አውሮፕላኖቹን መጠቀም ምርታማነትን ከመጨመርም ባለፈ በኋላቀር ርጭት አማካኝነት የሚከሰቱ ችግሮችን በመፍታት አዎንታዊ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጸዋል።

አውሮፕላኖቹ ሰፋፊ እርሻዎችን ተደራሽ ለማድረግ እጅግ ወሳኝ ናቸው ብለዋል።

አውሮፕላኖቹ አገልግሎት የሰጡባቸው ወረዳዎች ባለሙያዎች እና አርሶ አደሮች እንዳመለከቱት፤ ለኬሚካል ርጭት ይባክን የነበረውን ጉልበት እና ጊዜ ማስቀረት ተችሏል።

በጥላሁን ይልማ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!