ዓለምአቀፋዊ ዜና

የዶናልድ ትራምፕ ልዩ መልዕክተኛ ከፕሬዚዳንት ፑቲን ጋር ተወያዩ

By Melaku Gedif

August 06, 2025

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የዶናልድ ትራምፕ ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር የሩሲያና ዩክሬን ጦርነት ማስቆም በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ረዳት ዩሪ ኡሻኮቭ ሁለቱ ወገኖች ጦርነቱን ማስቆም በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ሀሳብ መለዋወጣቸውን ገልጸዋል፡፡

ልዩ መልዕክተኛው ከፕሬዚዳንት ፑቲን ጋር የነበራቸውን ውይይት ለፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ካደረሱ በኋላ በዋሽንግተን እና ሞስኮ መካከል ተጨማሪ ድርድሮች እንደሚደረጉ ጠቁመዋል።

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በ10 ቀናት ውስጥ ሩሲያ እና ዩክሬን ተኩስ አቁም እንዲያደርጉ ቀነ ገደብ በመስጠት ሩሲያ የማትስማማ ከሆነ በሞስኮና በነዳጅ ግብይት ሼሪኮቿ ላይ ማዕቀብ እንደሚጥሉ ማሳሰባቸውም ይታወሳል፡፡

በኔቶ የአሜሪካ አምባሳደር ማቲው ዊትከር የልዩ መልዕክተኛው ጉብኝት የሩሲያ እና ዩክሬንን ጦርነት ሊያስቆም እንደሚችል ያላቸውን ተስፋ መግለፃቸውን ቢቢሲ እና አር ቲ ዘግበዋል፡፡

በሚኪያስ አየለ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!