አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 75 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ገቢ አገኘ፡፡
የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አሸብር ባልቻ (ኢ/ር) የተገኘው ገቢ በበጀት ዓመቱ የተመረተውን ኃይል በመሸጥ እና ከተጓዳኝ አገልግሎቶች መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ 93 በመቶው ኃይል ለሀገር ውስጥ እንዲሁም 7 በመቶው ለውጭ ሽያጭ መቅረቡን አብራርተዋል፡፡
ለውጭ ሽያጭ ከቀረበው ኃይል 338 ነጥብ 7 ሚሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱን አንስተው÷ ለሀገር ውስጥ ገበያ ከቀረበው ደግሞ ከ28 ቢሊየን ብር በላይ ማግኘት መቻሉን አመልክተዋል፡፡
ተቋሙ ኃይል የማመንጨት ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ጠቁመዋል፡፡
በይሥማው አደራው
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!