አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሐረሪ ክልል በ5 ሚሊየን የኢትዮጵያ ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ስልጠና ከ13 ሺህ በላይ ዜጎች እየተከታተሉ ነው አለ የክልሉ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ።
የኤጀንሲው ኃላፊ ጀማል ኢብራሒም በክልሉ 27 ሺህ ወጣቶችን ለማሰልጠን እየተሠራ ይገኛል ብለዋል።
ስልጠናውን ተከታትለው እያጠናቀቁ ያሉ ዜጎችም በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያለውን የምስክር ወረቀት እየወሰዱ እንደሆነ አመልክተዋል።
ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ እንዲሁም የዲጂታል ክህሎት ለማሳደግ በሰው ሀብት ላይ መስራት እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
የቴክኖሎጂ እውቀቱ የዳበረ ትውልድ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን የሚፈታና የአገልግሎት አሰጣጥን የሚያዘምን ይሆናልም ነው ያሉት።
ኤጀንሲው የ5 ሚሊየን የኢትዮጵያ ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ስልጠናን ከክልሉ ትምህርት ቢሮ፣ ከስራና ክህሎት ቢሮ፣ ከኮሌጆችና ከኢትዮ ቴሌኮም እንዲሁም ከመብራት ኃይል ጋር በመሆን ስልጠናውን ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል።
የ”5 ሚሊየን ኢትዮጵያውያን ኮደርስ’’ ስልጠና ሐምሌ 2016 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይፋ መደረጉ ይታወሳል።
በየሻምበል ምህረት
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!