ስፓርት

ጀምስ ማዲሰን ለበርካታ ወራት ከሜዳ እንደሚርቅ ተረጋገጠ

By Hailemaryam Tegegn

August 07, 2025

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቶተንሀም ሆትስፐር አማካይ ጀምስ ማዲሰን ባጋጠመው ጉዳት ምክንያት ለበርካታ ወራት ከሜዳ እንደሚርቅ ክለቡ አረጋግጧል፡፡

ተጫዋቹ ባጋጠመው ጉዳት ከስድስት እስከ ሰባት ወራት ከሜዳ ሊርቅ ይችላል ተብሏል፡፡

የ28 ዓመቱ እንግሊዛዊ ጉዳቱ ያጋጠመው ከቀናት በፊት ቶተንሃም ከኒውካስል ዩናይትድ ጋር ባደረገው የቅድመ ውድድር ዘመን ጨዋታ ላይ ነው፡፡

ማዲሰን ቀዶ ህክምናውን በሚቀጥሉት ቀናት የሚያደርግ ሲሆን፥ ከጉዳቱ በፍጥነት እንዲያገግም ክለቡ መልካም ምኞቱን ገልጾለታል፡፡