አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ቪያሪያል የአርሰናል የመሀል ሜዳ ተጫዋች የነበረው የቶማስ ፓርቴን ዝውውር አጠናቅቋል።
ቪያሪያል የ32 ዓመቱን የቀድሞ የመድፈኞች ተጫዋች ቶማስ ፓርቴ በነጻ ዝውውር የግሉ ማድረግ ችሏል።
ጋናዊው ተጫዋች በነጻ ዝውውር የስፔኑን ክለብ የተቀላቀለ ሲሆን÷ ለሁለት ዓመታት የሚያቆየውን ኮንትራት መፈራረሙን ዘ አትሌቲክ ዘግቧል፡፡
በፈረንጆቹ 2020/21 የውድድር ዓመት ከአትሌቲኮ ማድሪድ ወደ አርሰናል የተዘዋወረው ፓርቴ 167 ጨዋታዎችን ለመድፈኞቹ አድርጓል፡፡
የስፔኑ ክለብ ቪያሪያል የቶማስ ፓርቴ ይፋዊ የፊርማ ሥነ ሥርዓት በቅርቡ ይፋ እንደሚደረግ ተመላክቷል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!