የሀገር ውስጥ ዜና

በአዋሽ ወንዝ ሙላት ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ድጋፍ ለማድረግ እየተሰራ ነው

By Adimasu Aragawu

August 07, 2025

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዋሽ ወንዝ ሙላት ለተፈናቀሉና ጉዳት ለደረሰባቸውን ዜጎች ድጋፍ ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል።

ሰሞኑን በጣለው ከባድ ዝናብ የአዋሽ ወንዝ በመሙላቱ በኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምዕራብ ሸዋ እና ምዕራብ ሸዋ ዞኖች የነዋሪዎች መኖሪያ ቤቶችና እርሻ መሬቶች ላይ ጉዳት አድርሷል።

በተለይም በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የዳዎ፤ ኢሉና ሰበታ ሀዋስ ወረዳዎች የሚገኙ ነዋሪዎች የጉዳቱ ሰለባ እንደሆኑና በምዕራብ ሸዋ ዞን ደግሞ የኤጀሬ፣ ኤጀርሳ ለፎና ወልመራ ወረዳዎች ነዋሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱ ተገልጿል።

የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ቡሳ ጎኖፋ ቅርንጫፍ ኃላፊ ገላኔ ሙለታ የወንዙ ሙላት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ከቀያቸው ማፈናቀሉንና ንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል።

በአደጋው ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ገልጸው÷ የክልሉ ቡሳ ጎኖፋ በቦታው ላይ በመገኘት ህይወት የማዳንና ለተፈናቃዮች ድጋፍ የማድረግ ስራ እያከናወነ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

በሁሉም አካባቢዎች ለተፈናቀሉና ጉዳት ለደረሰባቸውን ዜጎች እገዛና ድጋፍ ለማድረግ የተቀናጀ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑንም አረጋግጠዋል።

የምዕራብ ሸዋ ዞን ምክትል አስተዳደሪ አበበ ጨመዳ በበኩላቸው÷ በዞኑ የወንዙ ሙላት ጉዳት ባደረሰባቸው ወረዳዎች ለተፈናቀሉ ድጋፍ የማድረግና ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎች ከጎርፉ ውስጥ የማውጣት ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝ አስረድተዋል።

በአሁኑ ወቅት ጊዜያዊ መጠለያ እየተዘጋጀ መሆኑን አንስተው÷ የተለያዩ የቁሳቁስ ድጋፎች እየተደረገ መሆኑንም ተናግረዋል።

ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች አጋር አካላትን ጨምሮ የተለያዩ ማህበረሰብ ክፍሎች አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉም ጥሪ ቀርቧል።

በፀሐይ ጉሉማ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!