አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቁ በትኩረት እየተሰራ ነው አለ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለኢትዮጵያ የልማት ጉዞ ቁልፍ የሆነውን ኃይል በስፋት በማምረት ለሀገር ውስጥና ለውጭ ሀገራት ሽያጭ እያቀረበ ይገኛል፡፡
የተቋሙ ዋና ሥራ አሥፈጻሚ አሸብር ባልቻ (ኢ/ር) እንዳሉት÷በቀጣይ የሃይል አቅርቦቱን በቂ እና አስተማማኝ ለማድረግ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ግንባታ እየተከናወነ ነው፡፡
አሁን ላይ የኢትዮጵያውያን አንድነት ማሳያ የሆነው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቁን አንስተዋል፡፡
በተመሳሳይ አሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ግንባታ ተጠናቅቆ ኃይል ወደ ግሪድ ማሥገባት ጀምሯል ነው ያሉት።
የኮይሻና የአይሻ 2 የነፋስ ኃይል ማመንጫዎች በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ በትኩረትና በቅንጅት እየተሰራ እንደሚገኝም አመልክተዋል፡፡
ተቋሙ የሕብረተሰቡን የኃይል ፍላጎት ለማሟላት የጀመራቸውን ሥራዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል ዋና ሥራ አስፈጻሚው አረጋግጠዋል፡፡
በሰለሞን ይታየው
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!