የሀገር ውስጥ ዜና

የአዲስ አበባ የኮሪደርና የወንዝ ዳር ልማቶች የማንሰራራት ዘመን አብሳሪዎች ናቸው – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

By Abiy Getahun

August 09, 2025

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ የኮሪደር እና የወንዝ ዳር ልማቶች ለመዲናችን አዲስ የታሪክ ምዕራፍ የከፈቱ፣ ደረጃውን የጠበቀ የክትመት ንጋት እና የማንሰራራት ዘመን አብሳሪዎች ናቸው አሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ደረጃቸውን የጠበቁ ከተሞች የሀገራት ስልጣኔ፣ የተፈጥሮ ሚዛን ጥበቃ፣ የሕዝቦች የእሳቤ ከፍታ አድማስ እና አጠቃላይ የልማት እንቅስቃሴዎች የሚነበብባቸው ገጾች ናቸው ብለዋል።

አዲስ አበባ በልጆቿ ብርቱ ክንዶች እየለማችና እየደመቀች፣ በነዋሪዎቿ ትጋት እየፈካች እና እየተዋበች በተግባር ስሟን እየሆነች ያለች ከተማ ናት ሲሉ ገልጸዋል።

የሀገራችንና የአፍሪካ መዲናችን የውበት ብቻ ሳይሆን የቀልጣፋ አገልግሎት፤ የመዝናኛ ብቻ ሳይሆን የምቹ ኑሮ፤ ከዚህም ባለፈ አጠቃላይ የሀገራችን ፈጣን ልማት የሚቃኝባት የዕድገታችን ማሳያ ናት ነው ያሉት።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!